Notice: Test mode is enabled. While in test mode no live donations are processed.
First Name *
Last Name
Email Address *
Already have an account? Login
Donation Total: $100.00
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ጌታችን በወንጌሉ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” (ማቴ። ፲፮፥፳፬) ያለውን ተግባራዊ ያደገች ገድለኛ ሰማዕት ስትሆን የቀደሙ አባቶቻችን ገድሏን በመጻፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ አድርገውልናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን ሰማዕትነትን የተቀበለችበት ቀን ይታሰባል፡፡
ቅድስት አርሴማ ሮማዊ መሰረት ያላት ሰማዕት ስትሆን እርሷ እና ሌሎች ሃያ ሰባት ባልደረቦችዋ የሰማዕትነት አክሊል የተቀዳጁ የመጀመሪያዎቹ የአርሜንያ ሰማዕታት እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ ።
ቅድስት አርሴማ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች ። ቤተሰቦቿ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሐፍ ይነግረናል ። ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ነበረች፡፡
“ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።”